የውጭ ሃገር የሥራ ስምሪት የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም የሚያስጥብቅ እንዲሁም በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ብቻ ሳይወሰን የሰለጠነ የሰው ሃይል ስምሪትን የሚያካትት እና የዘመነ አገለግሎት እንዲሆን ባስቀመጥነው የሪፎርም አቅጣጫ መሰረት ወደ አውሮፓ (Sweden and Norway) ገበያ ለመግባት ቀደም ብሎ በተጀመረ ጥረት የዝግጅት ምዕራፍ ተጠናቆ ወደ ተግባር ተገብቷል። በመሆኑም በስምምነቱ መሰረት የተጠየቁ የሞያ ዘርፎች የሚከተሉት ናቸው።
1- ካርዲዬሎጂስት
2- የማርኬቲንግ ባለሙያ
4- ኬሚካል ኢንጅነር
5- ባስ ድራይቨር
6- አርክቴክት
7- አካውንታን
8- አውቶሞቲቭ ቴክኒሽያን ባለሙያ
9- የላብራቶሪ ቴክኒሺያን
10- የአይ ቲ ባለሙያ
11- የፋርማሲ ባለሙያ
12- የሽያጭ ባለሙያ
13- የሶፍትዌር ባለሙያ
14- ሜዲካል ዶክተር
15- የኮምፒተር ጥገና ባለሙያ
16- ነርስ
17- ግራፊክስ ዲዛይነር
18- የፀጉር ባለሙያ
19- የደንበኛ አገልግሎት ባለሞያ
በመሆኑም አስፈላጊውን ስልጠና እና ሌሎች መመዛኛዎችን በሟሟላት የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ዜጎች በኢትዮጲያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ( https://lmis.gov.et ) በመመዝገብ የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንድትሆን ጥሪ እናቀርባለን።
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
ማሳሰቢያ:
ከዚህ የስራ ዕድል ጋር ተያይዞ ግለሰቦች ከቴልግራም ግሩብ ላይ የተጠቀሰውን የመንግስት ተቋም (Ministry of Labor & Skills) በመወከል እነሱ እንደሚጨርሱላችሁ በግል ቢያናግሯችሁ በጭራሽ ፈቃደኛ እንዳትሆኑ ፡፡ ይህን ውል የተዋዋለው የኢትዮጵያ መንግስትና (Ministry of Labor & Skills) የተጠቀሱት ሀገራት (Sweden and Norway) ናቸው ፡፡ ስለዚህ ከናንተ ሚጠበቀው የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ ከሆነ በተቀመጠው ድህረ ገፅ በመመዝገብ የሚሰጣችሁን መመሪያ ተከታትሎ መፈፀም ነው ፡፡
OFFICIAL LINK: https://lmis.gov.et
ምንጭ፡ Muferihat Kamil Ahmed - The Ministry of Labor & Skills:👇