ወደ ውጪ ሃገራት ለሥራ መሰማራት ለምትፈልጉ በሙሉ: For all those who want to work abroad

ወደ ውጪ ሃገራት ለሥራ መሰማራት ለምትፈልጉ በሙሉ: For all those who want to work abroad

 መልካም ዜና 

በሦስት/3 የተለያዩ የስራ አይነቶች ወደ ውጪ ሃገራት ለሥራ መሰማራት ለምትፈልጉ በሙሉ!

    1.  በአሽከርካሪነት | by driving 
    2.  በቤት ውስጥ ሥራ Homework
    3.  በምግብ አብሳይነት As a cook


የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills

1. በአሽከርካሪነት ወደ ውጪ ሃገራት ለሥራ መሰማራት ለምትፈልጉ በሙሉ! | For those who want to work as a driver abroad

- በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (E-LMIS) ለሥራ ስምሪት የተመዘገባችሁ በአሽከርካሪነት ሥራ ወደ ውጪ ሃገራት ለመሰማራት የሚጠበቅባችሁን ስልጠናና የምዘና ፈተና በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት(TI) ስር በሚገኘው የአሸከርካሪ ማሰልጠኛ እና በሰላም ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ውስጥ ባለው ምሳሌ የመንጃ ፈቃድ ማሰልጠኛ ስልጠናችሁን ወስዳችሁ የምዘና ፈተና (COC) መጨረስ ትችላላችሁ፡፡ 

* Those who are registered for employment in the Ethiopian Labor Market Information System (E-LMIS) of the Ministry of Labor and Skills, the training and assessment test required to work as a driver in foreign countries. You can complete your training and pass the COC. 

በኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (E-LMIS) ላይ ያልተመዘገባችሁ እና በሹፍርና ሥራ ወደ ውጪ ሃገራት መሰማራት የምትፈልጉ በዚህ የድህረገጽ አድራሻ https://lmis.gov.et ሲስተም ላይ በመመዝገብና የባዮሜትሪክስ መረጃ በመሥጠት ሥልጠና እና የምዘና ፈተና መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ 

* We would like to inform you that those who are not registered on the Ethiopian Labor Market Information System (E-LMIS) and who want to work as drivers and work abroad can register on this website address https://lmis.gov.et and take training and assessment tests by providing biometric information.

አድራሻ Address:

የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት(TI) - ላምበረት የሥራና ክህሎት ሚንስቴር ዋናው መስሪያ ቤት አጠገብ |  Federal Technical and Vocational Training Institute (TI) - Lambert near Ministry of Jobs and Skills Headquarters.

-  ምሳሌ የመንጃ ፈቃድ ማሰልጠኛ - ኮተቤ ሃና ማሪያም አካባቢ የሚገኘው |  Example driving license training * located in Kotebe Hana Mariam area   

      - ሰላም ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ውስጥ |  Hello technical and vocational college    


- የቤት ውስጥ ሥራ ሞግዚትነት እና ፅዳት |  Housework babysitting and cleaning   

 2. በቤት ውስጥ ሥራ ወደ ውጪ ሃገራት መሰማራት ለምትፈልጉ በሙሉ! | For all those who want to work at home abroad!

- በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት E-LMIS  በውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት የተመዘገባችሁ በቤት ውስጥ አጋዥነት፣ ሞግዚትነት እና በፅዳት ሙያ መሰልጠን የምትፈልጉ ከ100 በላይ በሆኑ ስልጠና እየሰጡ ከሚገኙ የመንግስት ቴክኒክና ሞያ ኮሌጆዎች በተጨማሪ ከዚህ በታች ባሉ ተቋማት ተመዝግባችሁ ስልጠናችሁን መጀመር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

* In addition to more than 100 government technical and vocational colleges that are providing training, we would like to inform you that you can start your training by registering in the institutions below.  

  •  በአዲስ አበባ- ምስራቅ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ:  | Addis Ababa- East Poly Technic College, 
              -ንፋስ ስልክ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ: Nfas Selk Poly Technic College, 

  •  በክልሎች- ወራቤ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ |  In the regions - Werabe Poly Technic College,  
              -መቀሌ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ | Mekele Poly Technic College

- በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ ያልተመዘገባችሁ  lmis.gov.et ላይ በመመዝገብ የባዮሜትሪክስ መረጃ ሰጥታችሁ ወደ ስልጠናው መግባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

* We would like to inform you that those who are not registered on the Ethiopian labor market information system can enter the training by registering on lmis.gov.et and providing biometric information.

3. በምግብ አብሳይነት በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት በምግብ አብሳይነት እና በመሳሰሉ ሙያዎች መሰማራት ለምትፈልጉ ዜጎች Employment abroad as a cook For citizens who want to work as a cook and other professions 

- በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለምቶ ተግባራዊ በተደረገው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት(E-LMIS) ተመዝግባችሁ በውጪ ሃገር የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን የምትፈልጉ በኢትዮጵያ ቱሪዝም ማሰልጠኛ (TTI) ተመዝግባችሁ ስልጠናውን መጀመር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። 

* We would like to inform you that those who want to benefit from job opportunities abroad can register in the Ethiopian Labor Market Information System (E-LMIS) implemented by the Ministry of Labor and Skills and start the training. 

አድራሻ Address:

- ሜክሲኮ ቡናናሻይ እና ገነት ሆቴል

P.O.Box: 4350 Addis Ababa, Ethiopia

ስልክ :(+251)11 530 81 21/26

+251 11 551 94 18

Official Link👉  https://lmis.gov.et/

Website: tti.edu.et

ምንጭ | Source: 

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር  | Ministry of Jobs and Skills 

- ለበለጠ መረጃ ከታች የተቀመጡትን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር   ማህበራዊ ድህረገፆች ይከታተሉ |  For more information, follow the social networks of the Ministry of Jobs and Skills listed below.

በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE

ቴሌግራም:- https://t.me/fdre_mols 

ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y 


የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት https://lmis.gov.et

Connect with us for updates and more:

Telegram- https://t.me/TeddyTechGraphics

መልካም ዕድል | Good Luck

Teddy

To make it clear the most important part of our business

Post a Comment

Previous Next

نموذج الاتصال